Search

የሆርቲካልቸር ልማቱ ለጥቅል ዓመታዊ ምርት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ላቅ ያለ ነው፡- ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)

ዓርብ ጥቅምት 14, 2018 40

የ2018 የመጀመሪያ 100 ቀናት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) 2.45 ሚሊዮን ሔክታር መሬት ላይ የሆርቲካልቸር ምርቶች እየለሙ መሆኑን አስታውቀዋል።
የሆርቲካልቸር ዘርፉ ልማት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፃር የ31.7 በመቶ ዕድገት እንዳለውም ሚኒስትሯ አመላክተዋል።
የሆርቲካልቸር ልማት ትልቅ እሴት ያለው እና ለሀገርም ሆነ ለአርሶ አደሩ ከፍተኛ ገቢ የሚያስገባ ልማት ነው ሲሉም አስረድተዋል።
የሆርቲካልቸር ልማት በጥቅል ዓመታዊ ምርት ላይ የሚያበረክተው በጎ ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን አንስተዋል።
በጌትነት ተስፋማርያም