Search

የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማነቆዎች በመለየት ትልቅ ለውጥ ማምጣት ተችሏል

ዓርብ ጥቅምት 14, 2018 44

የኢንዱስትሪ ዘርፉን ማነቆዎች በመለየት የተሰሩ ሥራዎች ትልቅ ለውጥ ማምጣታቸውን የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሚልኬሳ ጃገማ (ዶ/ር) ገለፁ።
ዋና ዳይሬክተሩ ከኤፍ ኤም 97.1 ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እድገት ያላሳየበትን ምክንያቶች በመለየት በተደረጉ የፖሊሲ እና የመመሪያ ለውጦች በዘርፉ አመርቂ ውጤት ማስገኘት መቻሉን ጠቅሰዋል።
ባለፉት ሰባት ዓመታት የአምራች ዘርፉን ለማጠናከር የተፈጠሩ መደላድሎችን በተገቢው መንገድ መጠቀም እንደሚያስፈልግም አንስተዋል።
በመደመር መንግሥት መፅሐፍ በግልጽ እንደተቀመጠው፣ አምራች ዘርፉን ለማጠናከር በፊት የነበረውን ስትራቴጂ በተገቢው መንገድ በማየት እና ያለውን አቅም በመፈተሽ የማጠናከር ሥራዎች መሰራታቸው ተገልጿል።
የአምራች ዘርፉ ሰፊ የሥራ ዕድል መፍጠሩን ገልጸው፤ ከአምራች ዘርፉ ወደ ውጭ ከተላከ ምርት ከ318 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አንስተዋል።
በቢታንያ ሲሳይ