Search

አዲሱ የአውሮፕላን ማረፊያ የኢትዮጵያን የአቪዬሽን ማዕከልነት የሚያጠናክር ነው፡- አምባሳደር ቲቦር ናዥ

ዓርብ ጥቅምት 14, 2018 26

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እያደገ የመጣውን የአቪዬሽን እንዱስትሪ ገበያ በማጥናት ፍላጎቱን ለማሟላት እና ተወዳደሪነቱን ለማጠናከር በ10 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በቢሾፍቱ እጅግ ዘመናዊ እና ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ከተማ ለመገንባት እንቅስቃሴ ጀምሯል።
በአየር መንገዱ የሚገነባው ይህ የአውሮፕላን ማረፊያ ኢትዮጵያን በአቪዬሽን ዘርፍ የአፍሪካ ማዕከል መሆኗን የሚያጠናክር ነው ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የቀድሞ አፍሪካ ጉዳዮች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት ቲቦር ናዥ ተናግረዋል።
ከኢቢሲ አዲስ ዳያሎግ ፕሮግራም ጋር ቆይታ ያደረጉት አምባሳደር ቲቦር ናዥ እንደሚሉት፣ አየር መንገዱ የኢትዮጵያ ትልቅ ሀብት ሲሆን ለዓመታት የሀገሪቱ ምልክት እና ጌጥ ሆኖ ቆይቷል።
አፍሪካን እርስ በእርስ እና ከዓለም ጋር በማገኛነት አንጋፋ የሆነው አየር መንገዱ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ፣ ለአየር መንገዱ ብቻ ሳይሆን ሌሎች አየር መንገደኞችም ይተርፋል ብለዋል።
የቢሸፍቱ ኢንተርናሽናል የአውሮፕላን ማረፊያ ግንባታው ዘንድሮ የሚጀመር ሲሆን ከ4 ዓመታት በኋላ ለማጠናቀቅ ታቅዷል።
በላሉ ኢታላ