ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን በመቻል የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ የሚያስችል በቂ የተፈጥሮ ሀብት እንዳላት የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ማንደፍሮ ንጉሴ (ዶ/ር) ገለጹ።
የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከሚከናወኑ ሥራዎች መካከል የግብርናው ዘርፍ ዋናውን ድርሻ እንደሚወስድ ጠቅሰው፤ አብዛኛው የህብረተሰብ ክፍል በግብርና ሥራ የተሰማራ መሆኑን አንስተዋል።
የግብርናው ዘርፍ አንድም መሬት ጾም አያድርም የሚለውን የመደመር መንግሥት መርህ በተግባር እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።
በምግብ ራስን በመቻል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጉዞ እየተፋጠነ መሆኑን ገልጸው፤ ለስኬቱም ሁሉም በትብብር እንዲሠራ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሀገሪቱ ያላትን ሰፊ የሰው ኃይል፣ የውሃ ሀብት፣ የሚታረስ መሬት እና ምቹ ሥነ-ምህዳር በመጠቀም፤ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ ከማምረት ዓመቱን ሙሉ ለማምረት የሚያስችል አቅም በመፍጠር ግብርናን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።
ኢትዮጵያ አሁን በያዘችው አካሄድ የምግብ ሉዓላዊነቷን በማረጋገጥ ድህነትን እና ተረጂነትን ታሪክ እንደምታደርገው ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ebcdotstream #foodsecurity #foodsovereignty #agriculture