ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር በመሆን የተጠናቀቀውን የሳር ቤት-ጀርመን አደባባይ-ጋርመንት እና ፉሪ አካባቢ የኮሪደር ልማት ሥራ ጎብኝተናል ብለዋል።
589 ሄክታር በላይ የሚሸፍነው ከባቢ ከካዛንቺስ ቀጥሎ ሰፊው የልማት ስፍራ ሆኗል ሲሉ ገልፀዋል።
ፕሮጀክቱ 16.5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፣ የ3 ኪሎ ሜትር ተጨማሪ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ብሎም 33 ኪሎ ሜትር የተዘረጋ የእግረኛ መንገድ አካትቷል ብለዋል።

የፕላዛዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የሕፃናት መጫወቻዎች እና 5.2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ ተከናውኗል ሲሉ አንስተዋል።
የመኪና ማቆሚያዎች፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ኃይል መሙያ ስፍራዎች፣ በግል እና የመንግሥት ተቋማት የተገቡ 1107 ሱቆች በልማት ሥራው የተሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።
የኮሪደር ልማቱ 50.5 ሄክታር አረንጓዴ ሥፍራ፣ የሕዝብ መጸዳጃዎች፣ 13.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መጋለቢያ መንገድ፣ 38 የአውቶቡስ እና ታክሲ መጫኛ-ማውረጃዎችን አካትቷል ሲሉ ገልፀዋል።
እንደዚህ ያሉት ሀገራዊ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ሥራዎች የኢኮኖሚ እንቅስቃሴውን ከማሳደግ ባሻገር የትራፊክ እንቅስቃሴን በማሻሻል፣ ማኅበራዊ መስተጋብርን በማጠንከር ደማቅ ለእንቅስቃሴ ምቹ እና ዘላቂነት ያላቸው የከተማ ሥፍራዎች በመፍጠር ረገድ ዐቢይ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።