Search

ባህር ኃይል የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ዝግጁ ነው - ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ

ቅዳሜ ጥቅምት 15, 2018 84

118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን “የማትደፈር ሀገር የማይበገር ሠራዊት” በሚል መሪ ሃሳብ ቢሾፍቱ በሚገኘው የባሕር ኃይል የስልጠና ማዕከል ተከብሯል።
በወቅቱ የባህር ኃይል አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ፤ ኢትዮጵያ ከ1948 ዓ.ም ጀምሮ የባህር ኃይል እንደነበራት ገልፀው፤ ባለፉት 30 ዓመታት ግን ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር በግፍ እንድትርቅ መደረጉን አብራርተዋል።
የለውጡ መንግሥት ከመጣ በኋላ ግን የባህር ኃይሉን መልሶ ለማቋቋም በስልጠና እና በሎጂስቲክስ በሠራው ጠንካራ ሥራ የባህር ኃይሉ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ማስከበር በሚችልበት ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
 
በምንተስኖት ይልማ