የሚተከሉ ችግኞች ቆጠራ የሚካሄደው በሳይንሳዊ መንገድ መሆኑን የብሔራዊ አረጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር ቴክኒክ ኮሚቴ የቴክኖሎጂ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ካሳሁን ገልጸዋል።
ክልሎች በራሳቸው ዕቅድ በመያዝ ቦታዎችን ሲለዩ ከዚህ ቀደም ያልተተከለበት ቦታ መሆኑ ተረጋግጦ ካርታ እንደሚሠራለት ባለሙያው ጠቁመዋል።
ተከላው ሲጀመር በእያንዳንዱ ሳይት ሪፖርተሮች እንደሚኖሩ የጠቀሱት አቶ ቴዎድሮስ፤ የተከላው ሂደት እና የተተከሉ ችግኞችን መጠን እንደሚገልጹ ተናግረዋል።
የመጣው ቁጥር ከተቀመጠው የመሬት ስፋት ጋር ተገናዝቦ በሳይንሳዊ መንገድ እንደሚሰላ እና ቁጥሩ ከተጠበቀው በላይም ሆነ በታች ሲሆን ሲስተሙ እንደማይቀበል ገልጸዋል።
በዚህም መሰረት በትክክል የተተከሉት ችግኞች ብዛት ተረጋግጦ ወደ ማዕከል ስለሚመጣ ምንም ዓይነት መዛነፍ እንደማይኖር ባለሙያው አረጋግጠዋል።
በለሚ ታደሰ