ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጠንካራ ሥራ በኋላ አሁን የኮይሻ ግድብ 128 ሜትር ከፍታ ላይ መድረሱን ተናግረዋል።
ኮይሻ የደረሰበት ከፍታ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሁን ካለበት የ145 ሜትር ከፍታ 17 ሜትር ብቻ የቀረው መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ለሀገራቸው የቆሙ ኢትዮጵያውያን ቀን እና ሌሊት በመሥራት ፕሮጀክቱን እዚህ ደረጃ ላይ ማድረሳቸውን ጠቅሰው፣ ከኢትዮጵያውያን ኅብረት እና ትብብር ውጪ ገንዘብ ስላለ ብቻ ይህን የመሰለ ሥራ እንደማይሳካ ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ሲሠራ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተሳትፎ ከሌለበት ውጤታማ እንደማይሆን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፣ ለኮይሻ እዚህ መድረስ የአካባቢው ማኅበረሰብ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አንስተው ምስጋና አቅርበዋል።
በሥራው ሂደት ኢትዮጵያ በርካታ ባለሙያዎች ያገኘችበት እንደሆነ እና ይህ ደግሞ የትም የማይገኝ ታላቅ ሀብት እንደሆነ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያወሱት።
በለሚ ታደሰ