Search

የብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች የተሳካ ጉዞ እያደረገ ነው - አቶ አደም ፋራህ

ቅዳሜ ጥቅምት 15, 2018 32

የብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፎች የተሳካ ጉዞ በማድረግ ቃልን በተግባር እያስመሰከረ ነው ሲሉ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና /ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ተናገሩ፡፡

በብልፅግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ የተሰጡ አቅጣጫዎችን አስመልክቶ የፓርቲው ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና /ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ በሰጡት ማብራሪያ፤ ብልፅግና ለኢትዮጵያ የሚመጥን ራዕይ በመያዝ በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና ለማረጋገጥ እየሰራ ያለ ፓርቲ ነው ብለዋል።

ፓርቲው በሁሉም ዘርፎች የተሳካ ጉዞ እያደረገ መሆኑን አንስተው፤ ባለፉት ዓመታት ለህዝብ ቃል የገባዉን በተግባር በመፈጸም ቃሉን በተግባር እያረጋገጠ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የኢኮኖሚ እድገትን በማረጋገጥ አካታች እና የህዝቡን ኑሮ የሚያሻሽል እንዲሆን ሰፊ ስራ መሰራቱንና በዚህም አመርቂ ዉጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።

የህዝቡን ኑሮ ለማሻሻል የተሰራው ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ አነስተኛ ይዞታ ያላቸውን አርሶ አደሮች ተጠቃሚ የሚያደረጉ ስራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል።

በነዚህ ስራዎች ከፍተኛ ዉጤት መመዝገቡን ያነሱት አቶ አደም፤ ለአብነት 2010 . ይመረት የነበረዉ 306.1 ሚሊዮን ኩንታል የሰብል ምርት፤ 2017 . ወደ 1.57 ቢሊዮን ኩንታል ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል።

በቢታንያ ሲሳይ

#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #prosperity