ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ 8 ሺህ 613 አመራሮች ላይ የዲሲፕሊን ርምጃ መወሰዱን የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት እና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ገለፁ።
ፓርቲው የወሰደው ርምጃ ከኃላፊነት ማንሳት፣ ከደረጃ ዝቅ ማድረግ እና ሽግሽግን ያካተተ መሆኑን አቶ አደም ተናግረዋል፡፡
ፓርቲው ቃል የገባዉን በተግባር እንዲያረጋግጥ በየደረጃው ያለዉ አመራር እና አባል በጥሩ ስነ-ምግባር ኃላፊነቱን በብቃት እንዲወጣ እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።
በቀጣይ የተሰጠውን ኃላፊነት በሚገባ በማይወጣ፣ ሕዝቡን በታማኝነት የማያገለግል፣ በብልሹ አሰራርና ሌብነት ውስጥ የተዘፈቀ አመራር ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡
በየደረጃው ያለዉ አመራር እና አባል በጥሩ ስነ ምግባር ኃላፊነቱን እንዲወጣ በዚህም የህዝብ ተጠቃሚነት እና ኑሮ እንዲሻሻል ስርዓት እንዲገነባ ፓርቲው በትኩረት እንደሚሰራ አቶ አደም አመልክተዋል።
አያይዘውም ሀገራዊ ምክክሩ እንዲሳካ ፓርቲው ሚናውን የሚወጣ መሆኑን ገልጸዋል።
ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ነጻ ሆኖ በህዝብ ታማኝነት ያለው ሆኖ እንዲካሄድና እንዲጠናቀቅ የብልፅግና ፓርቲ የድርሻውን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆኑን አቶ አደም ተናግረዋል።
በቢታንያ ሲሳይ
#ebc #ebcdotstream #Ethiopia #prosperity