Search

የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዘላቂ ሰላም በትብብር መሥራታቸውን አጠናክረው መቀጠል ይገባቸዋል

እሑድ ጥቅምት 16, 2018 51

የአማራ ክልል መንግሥት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት የምክክር መድረክ በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዋና ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በውይይቱ እየተሳተፉ ነው።

የመድረኩ ዓላማ በፓርቲዎች መካከል ጤናማ የሆነ ግንኙነት ፈጥሮ በየጊዜው እየተገናኙ በመወያየት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በክልሉ ያለው የሰላም እና ፀጥታ ሁኔታ ከጊዜ ጊዜ መሻሻል ያሳየ ቢሆንም፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለዘላቂ ሰላም በትብብር መሥራታቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው ተጠቁሟል።

በተስፋሁን ደስታ

#ebcdotsteram #bahirdar #government #politicalparties