የኮይሻ ፕሮጀክት አቅምን እንዴት ወደ ጥቅም መቀየር እንደሚቻል በደንብ ያሳየ ነው ሲሉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 100 ቀናት የማክሮ ኢኮኖሚ አፈፃፀም ግምገማን በኮይሻ ግድብ ከሚኒስትሮች ጋር አካሂደዋል።
ዶ/ር ኤርጎጌ፥ የኮይሻ ኘሮጀክት በአንድ ወቅት ቆሞ እንደነበር አስታውሰው፤ ነፍስ ዘርቶ አሁን ካለበት ደረጃ እንዲደርስ የተሰጠው ቁርጠኛ አመራር የሚደንቅ እንደሆነ ነው የገለጹት።

ተርባይኖች ከዚህ ቀደም ከውጭ ይገዙ እንደነበር አንስተው፤ ለኮይሻ ግድብ ግን ተርባይኖች በሀገር ውስጥ መመረታቸው እያደገ ያለውን የውስጥ አቅም ያሳየ ነው ብለዋል።
በተጨማሪም ለግድቡ ግንባታ የሚውለው አብዛኛው ግብዓት ከአካባቢው የተገኘ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የውጭ ምንዛሬ ወጪን ለመቀነስ ማስቻሉን ተናግረዋል።
ይህም በአግባቡ ከተገለገልንባቸው የየአካባቢውን ማኅበረሰብ ከመጥቀም አልፈው ለሀገራዊ ዕድገታችን መሠረት የሚሆኑ ያላስተዋልናቸው በርካታ ሀብቶቻችንን እንድናይ ዓይናችንን የገለጠ ነው ብለዋል።
በሜሮን ንብረት
#ebcdotstream #ethiopia #koysha