በሆሳዕና ከተማ በኮሪደር ልማት አማካኝነት ዘመናዊ የእግረኛ መንገዶች እና የተለያዩ መዝናኛ ስፍራዎች እየተገነቡ ነው።
የኮሪደር ልማት ከተማችን አዲስ ገፅታ እና የሥራ ባህል እንድትላበስ አስችሏታል ሲሉ የሆሳዕና ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት የአገልግሎቶች ፅ/ቤት ዋና ሥራ አስፈፃሚ ደሳለኝ ደፋር ተናግረዋል።

በአጠቃላይ 35 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የኮሪደር ልማቱ ግንባታ ለማካሄድ መታቀዱን የገለጹት አቶ ደሳለኝ፤ በመጀመሪያው ዙር ግንባታ 24.5 ኪሎ ሜትር የሚሆነውን በፌደራል እና በራስ አቅም መሸፈኑንም አስረድተዋል፡፡
ቀን እና ሌሊት እየተካሄደ ያለው ልማቱ ከተማዋ ከዚህ ቀደም ያልነበራትን የመኪና ማቆሚያ ፣የሕዝብ ትራንስፖርት መጫኛ እና ማውረጃ፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች እንዲኖራት ማስቻሉንም ነው የገለፁት፡፡
በአፎሚያ ክበበው