6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል።

በመደበኛ ስብሰባው ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ያደረጉትን የመክፈቻ ንግግር አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራሪያ ይሰጣሉ።
ምክር ቤቱ የመንግሥትን አቋም በማዳመጥ የድጋፍ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ኢቢሲ የስብሰባውን ሙሉ ሂደት ኢቲቪ ፓርላማ ቻናልን ጨምሮ በሁሉም የብሮድካስት እና የዶትስትሪም ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች በቀጥታ እያስተላለፈ ይገኛል፤ እንዲከታተሉ ጋብዘንዎታል።