Search

የኮሪደር ልማት የቦታ እና ጊዜ ምልከታን የሚቀይር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማክሰኞ ጥቅምት 18, 2018 57

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል እየተተገበረ ያለውን የኮሪደር ልማት በተመለከተ ባነሡት ሐሳብ፣ “የኮሪደር ልማት የቦታ እና ጊዜ ምልከታን የሚቀይር ነው” ብለዋል።
ለአብነትም በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ ሺህ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራ መገንባቱን ጠቅሰው፣ በርካታ ወጣቶች ወደ ስፖርት እየተመለሱ መሆኑን እና ይህም ማኅበረሰብን የመገንባት ሥራ እንደሆነ ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማት የትውልድ ሥነ ልቦና ስብራትን እያረቀ ያለ ሥራም ጭምር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ይህን ማንም ሰው የሚያየው፣ ማንም ሰው የሚናገረው ጉዳይ እንደሆነ ጠቁመዋል።