የኮሪደር ልማቱ የኮንፈረስ ከተማ የሆነችውን አዳማን ውብ ገጽታ ከማላበሱ ባለፈ፣ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረገ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ኃይሉ ጀልዱ ገልጸዋል።

ልማቱ እውን ሊሆን የቻለው በላቀ የሕዝብ ተሳትፎ ነው ያሉት ከንቲባው፤ የተገነቡትን መሠረተ ልማቶች መጠበቅ እና መንከባከብ እንደሚገባ ተናግረዋል።
በቀጣይም ከተማዋን ውብ እና ተመራጭ፣ ለነዋሪዎቿም ምቹ እና ተስማሚ እንድትሆን እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

የኮሪደር ልማቱ የተለያዩ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ የብስክሌት መንገዶች እና መጸዳጃዎችን ያካተተ ሲሆን፣ እነዚህም ለከተማዋ ነዋሪዎች ምቹ ተደርገው መሠራታቸው ተገልጿል።
የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው የኮሪደር ልማቱ ከተማዋን ልዩ ውበት እዳጎናጸፋት ገልጸው፤ የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን መጠበቅ ደግሞ የእኛ ኃላፊነት ነው ብለዋል።
በሰናይት ብርሃኔ