Search

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቻፓ ኩባንያ ጋር በአጋርነት ለመሥራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

ሓሙስ ጥቅምት 20, 2018 54

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከቻፓ ኩባንያ ጋር በአጋርነት መሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ዛሬ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል ተፈራርሟል።

የመግባቢያ ስምምነቱን የኢትዮጵያ አየር መንገዱ ግሩፕ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኃይለመለኮት ማሞ እና የቻፓ ኩባንያ መሥራቾች ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሠረት ቻፓ ኩባንያ ደንበኞች በኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ-ገፅ ላይ በሁሉም የክፍያ አማራጮች የቲኬት ግዢ አገልግልት እንዲያገኙ ያስችላል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ኃይለመኮት ማሞ፥ ከቻፓ ኩባንያ ጋር የተደረገው ስምምነት ደንበኞች በአንድ ፕላትፎርም በቀላሉ የቲኬት ግዢ መፈፀም እንዲችሉ የሚያደርግ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም አየር መንገዱ ከቻፓ ኩባንያ ጋር በትብብር ለመሥራት ያደረገው ስምምነት የሀገር ውስጥ የቴክ ኩባንያዎች እንዲጠናከሩ እንደሚረዳም ነው የገለጹት።

የቻፓ ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ናኤል ኃይለማርያም፥ የአየር መንገዱ ደንበኞች የኤቲኤም ካርድ ቁጥርን በመጠቀም ያለ ማሽን ክፍያ መፈፀም እንደሚችሉ ተናግረዋል። 

ኩባንያው ወደፊት ኢትዮጵያውያን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ማንኛውንም ምርት እና አገልግሎት እንዲገዙ የሚያስችል አሠራር ለመፍጠር ሕልም እንዳለው ገልጸዋል።

በሁለት ኢትዮጵያውያን ትጋት ከ4 ዓመታት በፊት የተመሠረተው ቻፓ ኩባንያ ከ60 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የሥራ ዕድል መፍጠሩም በመድረኩ ተገልጿል።

በላሉ ኢታላ

#ebcdotstream #Ethiopia #ethiopianairlines #eal #chapa