Search

የብዝኀ ዘርፍ ኢኮኖሚ መርህን መከተል ኢኮኖሚው በከፍተኛ ጫና ውስጥ እንዳይወድቅ ያስችላል

ሓሙስ ጥቅምት 20, 2018 32

የብዝኀ ዘርፍ ኢኮኖሚ መርህን መከተል ኢኮኖሚው በከፍተኛ ጫና ውስጥ እንዳይወድቅ ያስችላል ሲሉ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ አሰፋ ሱሞሮ ገለጹ።

አቶ አሰፋ ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአንድ ዘርፍ ላይ የተመሠረተ እንደነበር ጠቅሰው፤ ይህም ለሀገር ዕድገት እንቅፋት እንደነበር ተናግረዋል።

የብዝኀ ዘርፍ ኢኮኖሚ መርህን መከተላችን ለበርካታ ዓመታት ከነበርንበት ችግር ለመላቀቅ ያስችለናል ነው ያሉት።

ይህን ሲያብራሩም፥ ኢኮኖሚያችን በብዝኀ ዘርፍ ላይ የተመሠረተ ከሆነ በኢኮኖሚው ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉ ጫናዎች ቀለል ያሉ ናቸው ብለዋል። 

በተጨማሪም የብዝኀ ዘርፍ ኢኮኖሚ መርህን መከተል ሀገራዊ ኢኮኖሚው እንዲያድግ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ገልጸው፤ አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢኮኖሚው ያጋጠሙትን ችግሮች ለመቅረፍ መንግሥት የተለያዩ እርምጃዎችን መውሰዱን ከፍተኛ አማካሪው አንስተው፤ ይህም ኢኮኖሚው እንዲያድግ አስችሎታል ብለዋል።

ሀገሪቱ ያጋጠማትን የማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ለማስተካካል መንግሥት በወሰደው የአጭር ጊዜ እርምጃ በርካታ ለውጦች መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ለአብነትም ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በመደረጉ ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

በሃይማኖት ከበደ

#ebcdotstream #ethiopia #economy # diversification