Search

የአሁኑን ድል ለየት የሚያደርገው ተላላኪዎቹን በዜሮ ኪሳራ በመደምሰሳችሁ ነው - ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ

ቅዳሜ ጥቅምት 22, 2018 112

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ ሰቀልት ወረዳ የባንዳነት ተልዕኮ ተቀብሎ የመጣው የፅንፈኛው ኃይል በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር በተወሰደበት እርምጃ ሙሉ ለሙሉ ተደምስሷል።

በግዳጅ ቀጣናው የተገኙት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፥ የደመሰሳችሁት የፅንፈኞች ስብስብ ባዳ ከሆኑ የሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች ጋር የሚሠራ ነው ብለዋል።

እርምጃው ባዳዎቹም ሆነ ባንዳዎቹ ቆም ብለው ሊያስቡ እንደሚገባ ትምህርት የሰጠ የማያዳግም እርምጃ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ክፍለጦሩ ድል ብርቁ አይደለም ያሉት ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ፤ የአሁኑን ድል ለየት የሚያደርገው ተላላኪዎቹን በዜሮ ኪሳራ በመደምሰሳችሁ ነው ብለዋል።

የፅንፈኛው ኃይል በተወሰደበት የማያዳግም እርምጃ ከ80 በላይ መደምሰሱን፣ ከ30 በላይ ምርኮኛ እና ቁስለኛ መሆኑን እንዲሁም በርካታ የነፍስ ወከፍ እና የቡድን መሳሪያ መማረኩን ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

#ebcdotstream #Ethiopia #ENDF #NorthwestCommand