Search

አርሰናል ሲያሸንፍ ማንችስተር ዩናይትድ አቻ ተለያየ

ቅዳሜ ጥቅምት 22, 2018 38

በ10ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሜዳው ውጭ ከበርንሌይ የተጫወተው አርሰናል 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
በተርፍሞር በተደረገው ጨዋታ ቪክቶር ዮኬሬስ እና ዴክለን ራይስ ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
መድፈኞቹ አሁንም መረባቸውን ሳያስደፍሩ የወጡ ሲሆን የሊጉን መሪነትም በ25 ነጥብ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ በውድድር ዓመቱ ባደረጋቸው 15 ጨዋታች ግብ የተቆጠረበት በሦስቱ ብቻ ነው፡፡
አርሰናል በሊጉ ካስቆጠራቸው 18 ግቦች 12ቱ የተቆጠሩት ከቆመ ኳስ ነው፡፡
ያለፉትን ሦስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ያሸነፈው ማንችስተር ዩናይትድ ከኖቲንግሀም ፎረስት ሁለት አቻ ተለያይቷል፡፡
በሲቲ ግራውንድ በተደረገው ጨዋታ ካስሜሮ እና አማድ ዲያሎ የዩናይትድን ግቦች አስቆጠረዋል፡፡
በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ኖቲንግሀም በ2ኛ አጋማሽ ሞርጋን ጊብስ ዋይት እና ሳቮና አከታትለው ባስቆጠሯቸው ግቦች ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል፡፡
ዩናይትድን ከተረከቡ ዛሬ 1ኛ ዓመታቸውን ያከበሩት አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም ለ4ኛ ተከታታይ ጊዜ የማሸነፍ ጉዟቸውም ተገቷል፡፡

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ:

ተያያዥ ዜናዎች: