Search

ኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት በግሎባል ጌትዌይ ስትራቴጂ ትግበራ ዙሪያ መከሩ

ማክሰኞ ጥቅምት 25, 2018 57

ግሎባል ጌትዌይ ስትራቴጂ በዲጂታል፣ በኃይል እና በትራንስፖርት ዘርፎች ንፁህ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ትስስርን ለማሳደግ ብሎም የጤና፣ የትምህርት እና የምርምር ሥርዓቶችን በዓለም ዙሪያ ለማጠናከር በአውሮፓ ኅብረት የተነደፈ ስትራቴጂ ነው።

ስትራቴጂው በፈረንሳይ፣ ፓሪስ በተካሄደው የኢትዮጵያ እና የአውሮፓ ኅብረት የንግድ ጉባዔ ላይ ዋና የውይይት ርዕሰ ጉዳይ ነበር ተብሏል።

የኢፌዴሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ከፍተኛ ልዑካን ከአውሮፓ ኅብረት እና ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ አመራሮች ጋር በመሠረተ ልማት፣ በኃይል፣ በዲጂታል ግንኙነት እና በአረንጓዴ ሽግግር ዘርፎች ስትራቴጂያዊ ኢንቨስትመንትን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ገንቢ ውይይት አድርገዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት፥ ኢትዮጵያ በግሎባል ጌትዌይ ስትራቴጂ ማዕቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እና ሁሉን አቀፍ ዕድገት ለማረጋገጥ በትብብር ለመሥራት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።

ውይይቱ በኢትዮጵያና በአውሮፓ ኅብረት መካከል በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እና ቀጣይነት ያለው የኢንቨስትመንት ትብብርን ለማጠናከር ሚናው የጎላ መሆኑም ነው የተገለጸው።

በሰለሞን ከበደ

#ebcdotstream #ethiopia #europe #investment #globalgateway