የአፍሪካ ባንግላዴሽ የንግድ ትርዒት እና የውይይት መድረክ በአዲስ አበባ ተከፈተ።
በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር ሲትዋት ናይም፥ ኢትዮጵያ እና ባንግላዴሽ ያላቸው ግንኙነት የጠበቀ ነው ብለዋል።
በዚህ የንግድ ትርዒት መድረክ የእውቀት ሽግግር ከመደረጉ ባለፈም፤ የባንግላዴሽ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ዕድል የሚከፍት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያዊያንም በባንግላዴሽ ንግድ ተሳታፊ እንዲሆኑ ያደርጋል ነው ያሉት አምባሳደር ሲትዋም ናይም።
በባንግላዴሽ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የንግድ እና ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እንዲሁም የንግድ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት፤ በተለያዩ ቁልፍ ሴክተሮች ላይ ያለውን ትብብር ማጠናከር ይገባል ያሉት ደግሞ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመካከለኛው ምሥራቅ ኤዥያ እና የፓስፊክ ሀገራት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ደዋኖ ከድር ናቸው።
የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዲኤታ ይድነቃቸው ወርቁ፥ ኢትዮጵያዊ ከማክሮ ኢኮኖሚ ትግበራ በኋላ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሆናለች ብለዋል።
በኤዶም አማረ