ዛሬ ጠዋት በአማራ ክልላዊ መንግሥት ኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር መቀመጫ በሆነችው ከሚሴ ተገኝቼ ለሕዝቡ መልዕክት አስተላልፌያለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
በአማራ ክልል ከጎበኘኋቸው ዞኖች እስከአሁን ያልጎበኘሁት ዞን በመሆኑ ጉብኝቱን የተለየ ያደርገዋል ብለዋል።

የከሚሴ የኮሪደር ልማት ሥራ በጅምር ደረጃ ያለ ቢሆንም የ1.3 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ እና የእግረኛ መንገድ ሥራዎች የሚመሰገኑ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል።
የኮሪደር ልማት ሥራ የሕዝባዊ ሥፍራዎችን ደረጃ ከፍ በማድረግ ዕሳቤ በሁሉም ደረጃ በመላው ኢትዮጵያ እየተተገበረ መሆኑን እንደሚያሳይ አንስተዋል።
በከተማዋ ለሌማት ትሩፋት ሥራችን አስተዋጽዖ እያበረከተ ያለውን የኤልፎራ አግሮ-ኢንዱስትሪ የተቀናጀ የግብርና ልማት ፋብሪካንም ጎብኝተናል ብለዋል።