Search

ጥልቅ አጋርነታችን በርካታ ቁልፍ ሰነዶችን በመፈረም ተጠናክሯል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ ኅዳር 10, 2018 157

ባለፈው ዓመት ወደ ማሌዥያ ኦፊሴላዊ ጉብኝት ካደረኩኝ አንድ ዓመት በኋላ፣ የማሌዥያ ፌዴሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂምን በኢትዮጵያ ተቀብያለሁ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ።
የጉብኝት ልውውጡ ጥልቅ አጋርነታችንን የሚመሰክር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፤ ይህም በርካታ ቁልፍ ሰነዶችን በመፈረም ተጠናክሯል ብለዋል።
 
የመግባቢያ ሰነዶቹ በቱሪዝም፣ በጤና፣ በአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በኳላ ላምፑር ከተማ ምክር ቤት እና በአዲስ አበባ አስተዳደር የትብብር መስክ ላይ ያተኮሩ ናቸው ሲሉ ገልፀዋል::
ባደረግነው የሁለትዮሽ ውይይት፣ ትብብራችንን የበለጠ ለማጠናከር እና ለማስፋት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት አረጋግጠናል ብለዋል።