Search

በኢትዮጵያ እና በማሌዥያ መካከል በተለያዩ መስኮች የትብብር ስምምነቶች ተደረጉ

ረቡዕ ኅዳር 10, 2018 142

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የማሌዢያ ፌደሬሽን ጠቅላይ ሚኒስትር ዳቶ ሰሪ አንዋር ቢን ኢብራሂምን በብሔራዊ ቤተ-መንግሥት በይፋዊ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ተቀብለዋል።
 
መርሀ-ግብሩ የወዳጅነት ዛፍ የመትከል ሥነ-ሥርዓት፣ የብሔራዊ ቤተ-መንግሥት ጉብኝት፣ የሁለትዮሽ ውይይት፣ የሰነዶች ልውውጥ ብሎም በቱሪዝም፣ በጤና፣ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ በኳላ ላምፑር ከተማ ምክር ቤት እና በአዲስ አበባ አስተዳደር የትብብር ስምምነቶችን ያካተተ ነበር።