Search

በቴሌብር ወይም በአዋሽ ባንክ ደመወዛቸውን የሚቀበሉ ሠራተኞች እስከ 1 ሚሊዮን ብር ብድር ማግኘት ይችላሉ

ሓሙስ ኅዳር 11, 2018 181

በቴሌብር ወይም በአዋሽ ባንክ ደመወዛቸውን የሚቀበሉ የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት ሠራተኞች እስከ 1 ሚሊዮን ብር ብድር ማግኘት እንደሚችሉ ተገለጸ።

ኢትዮ ቴሌኮም ከአዋሽ ባንክ ጋር በመተባበር በቴሌብር አማካኝነት የሚተገበር "ጥላ" የተሰኘ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን አስጀምሯል።

አገልግሎቱን ያስጀመሩት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እና የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንት ፀሐይ ሽፈራው  ናቸው።

በቴሌብር አማካኝነት  የሚጀመረው "ጥላ" የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት የቁጠባ እና ብድር አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፤ በውስጡ ሌሎች ዘርፈ ብዙ ተጨማሪ አገልግሎቶችን እንደያዘ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገልጸዋል።

ለአብነትም አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርኘራይዞች 6 ወር የሚከፈል እስከ 150 ሺህ ብር የሚደርስ የብድር አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ።

በሌላ በኩል የመንግሥትም ሆነ የግል ተቋማት ሠራተኞች በቴሌ ብር ወይም በአዋሽ ባንክ ደመወዛቸውን የሚቀበሉ ከሆነ፤ 6 ወር ደመወዛቸውን ያህል ወይም እስከ 1 ሚሊዮን ብር በመበደር ይህንኑ 16 ወራት መመለስ ይችላሉ።

አዋሽ ባንክ ለዚህ አገልግሎት የሚውል 2 ቢሊዮን ብር ለብድር ማዘጋጀቱ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል።

የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት ያልቻሉ የህብረተሰብ ክፍሎችም ዘኔክሰስ ጨምሮ ስማርት ስልኮችን "በጥላ" አማካኝነት በብድር በመግዛት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ  የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳት ፀሐይ ሽፈራው አስታውቀዋል።

በኤዶሚያስ ንጉሴ

#ebcdotstream #ethiotelecom #awashbank #telebirr #digitalfinance