Search

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካን መጻኢ የታዳሽ ኃይል ተስፋ የሚያመላክት ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

እሑድ ኅዳር 14, 2018 110

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የአፍሪካን መጻኢ የታዳሽ ኃይል ተስፋ የሚያመላክት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ኢትዮጵያ ከውሃ በተጨማሪ በፀሐይ፣ ንፋስ፣ እንፋሎት እና በኒውክሊየር የታዳሽ ኃይል ምንጮች ላይ እየሠራች ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትናንት በቡድን 20 የመሪዎች ጉባዔ ላይ ላይ ባደረጉት ንግግር።

ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢንዱስትሪ ዘርፍን ለማነቃቃት የሚያስችል ከብክለት ነጻ የሆነ የታዳሽ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር እየዘረጋች እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በሀገሪቱ የብሔራዊ መታወቂያ አገልግሎትን ጨምሮ ዲጂታል የመረጃ እና የክፍያ ሥርዓትን በማስፋፋት ሕዝባዊ አገልግሎትን ለማዘመን እየተሠራ መሆኑንም አንስተዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂን ድርቅን መተንበይ፣ በሽታዎችን መለየት እና አካባቢያዊ ቋንቋዎችን መተርጎምን ጨምሮ አካታች በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ ለማዋል እየተከናወነ ያለውን ሥራም አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ለሌሎች ሀገራት የምታጋራቸው በርካታ ስኬታማ ተሞክሮዎች እንዳሏት የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሆኖም ቀጣይነት ያለው አካታች ዕድገት እንዴት ማስመዝገብ እንደሚቻል ከእኛ መማር ይቻላል ብለዋል።

በመሐመድ ፊጣሞ

#ebcdotstream #G20 #Johannesburg #PMAbiyAhmed #Ethiopia