Search

የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ለመመለስ ምን ተሰራ?

ማክሰኞ ኅዳር 16, 2018 57

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት በመንግሥት፣ በበጎ ፈቃድ (ኢኒሼቲቭ) እና በግል ገንቢዎች (አልሚዎች) ትብብር በርካታ ቤቶችን በመገንባት በፍትሐዊነት ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገልጿል፡፡
በዚህም በተለያዩ አማራጮች ቤቶችን በመገንባት፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትን በማሻሻል አመርቂ ውጤቶች መገኘቱ ተጠቅሷል፡፡
በከተማ አስተዳደሩ እስካሁን ድረስ በተለያዩ ፕሮግራሞች የተከናወነው የቤት ልማት ዝርዝር ቀጥሎ ቀርቧል፦
👉በኮንዶሚኒየም ፕሮግራም - 139 ሺህ 8
👉ለአቅመ ደካሞች እና ለአገር ባለዉለታዎች (በመንግስት እና በበጎ
👉ፈቃደኞች ትብብር የተገነቡ) - 40 ሺህ 576
👉በከተማ አስተዳደር ለኪራይ የተገነቡ - 24 ሺህ 819
👉በሪል እስቴት፣ በማህበር እና በግል ገንቢዎች የተገነቡ - 175 ሺህ 605
👉በድምሩ ከ380 ሺህ በላይ የሚሆኑ ቤቶች ለተጠቃሚዎች ተላልፈዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ በቀጣይም የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመመለስ በትኩረት እንደሚሰራ ከከተማዋ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡