Search

በ93ኛው የኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ያለችው ኢትዮጵያ

ማክሰኞ ኅዳር 16, 2018 64

በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ /ሚካኤል የተመራኢትዮጵያ ልዑክ በሞሮኮ፣ መራኬሽ ከተማ .. ከኅዳር 24 እስከ 27 ቀን 2025 እየተካሄደ በሚገኘው 93ኛው የኢንተርፖል ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ /ሚካኤል ከጉባኤው ጎን ለጎን ከሞሮኮ ብሔራዊ ደኅንነት ጄነራል ዳይሬክተር አብዱልለጢፍ ሃሙቺ ጋር ሁለቱ የሕግ አስከባሪ ተቋማት በትብብር መሥራት የሚያስችላቸው የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል።

የሁለቱ ሀገራት የሕግ አስከባሪ አካላት የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል እንዲሁም በስልጠና እና በፀጥታ ማስከበር በትብብር ለመሥራት የሚያስችል መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መረጃ ያመለክታል

#ebcdotstream #Ethiopia #Interpol #Morocco #Marrakech