Search

አፈርን የሚያክመው የተፈጥሮ ማዳበሪያ እንዴት ይዘጋጃል?

የተፈጥሮ ማዳባሪያ (ኮምፖስት) የአፈር አካላዊና ሥነ ሕይወታዊ ጤንነትን በመጠበቅ ለተክሎች ጤናማ እድገትና ምርታማነት ከፍተኛ ድርሻ አለው፡፡
በተለይ በከፍተኛ አሲዳማነት ለተጠቃ የእርሻ መሬት አሲዳማነትን በመከላካል ረገድ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ይገለጻል፡፡
የኬሚካል የአፈር ማዳበሪያ በአፈር ላይ የሚያደርሰውን ጉዳት ለመከላከልም ኮምፖስትን ቀላቅሎ መጠቀምን ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
የተፈጥሮ ማዳበሪያ ለተክሎች አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ለመስጠት፣ የአፈር ለምነትን፣ የውኃ መያዝ ችሎታን እንዲሁም የሰብልና ፍራፍሬ ምርቶችን ለመጨመር ያስችላል፡፡
ለመሆኑ የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት) እንዴት ይዘጋጃል?
በቀዝቃዛ አካባቢዎች የመብላላቱን ሂደት ለማፋጠን በጉድጓድ ውስጥ ይዘጋጃል፤ በሞቃታማ አካባቢዎች ደግሞ ከመሬት በላይ ግብዓቶችን በመከመር ማዘጋጀት ይቻላል፡፡
ኮምፖስት ሊበሰብሱ ከሚችሉ ፍራፍሬዎች፣ ተክሎች፣ የምግብ ትርፍራፊዎች እንዲሁም ከሳር በል እንስሳቶች ፍግ አየር ባለበት ሁኔታ የሚዘጋጅ ነው፡፡
የተፈጥሮ ማዳበሪያ ሲዘጋጅ መካተት የሌለባቸው ግብአቶች የትኞቹ ናቸው?
ዘር ያፈሩ የአረም ተክሎች፣ የባሕርዛፍ የቅጠል ርጋፊዎች፣ የተለያዩ ቀለማትን የያዙ ወረቀቶች፣ የከሰል አመድ፣ በበሽታ የተጠቁ እፅዋቶች፣ ሥጋ በል የሆኑ የቤት እንስሳቶች እዳሪ እንዲሁም ሰው ሰራሽ ኬሚካሎች መካተት የለባቸውም፡፡
ከዚህ በተጨማሪ የማይበሰብሱ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች፣ ስጋ፣ አጥንት፣ የአሳ ግልፋፊዎች፣ የወተት ተዋጽዖዎች የመሳሰሉት መካተት የለባቸውም፡፡
ከላይ የተጠቀሱትን በኮምፖስቱ ውስጥ ማካተት ለሰው ልጅ ጤና ጠንቅ ከመሆን ባለፈ የማብላላት ሂደቱን ሊያዘገዩ እና ለተክሎቹም መርዛማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ባለሙያዎች ይመክራሉ፡፡
በማስተዋል መታፈሪያ