ጣና ነሽ ፪ ጀልባ የመጀመሪያውን የመንገደኞች ማጓጓዝ ከባሕር ዳር ወደ ደልጊ እና ደቅ በማድረግ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀምራለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጣና ነሽ ፪ ጀልባን በጎርጎራ ሥራ አስጀምረው ወደ አገልግሎት መግባቷ የሚታወስ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ጣና ነሽ ፪ ጀልባ “የጣና ውሃን እየቀዘፈች ባሕር ዳር ከተማን ከጎርጎራ ኢኮ ሎጅ ማገናኘት ጀምራለች” ማለታቸውም ይታወሳል።

188 ተሳፋሪዎችን የማጓጓዝ አቅም ያላት ጣናነሽ ፪ በአስደማሚው የጣና ሐይቅ የተፈጥሮ ከባቢ የሚደረገውን ጉብኝት እና ወደ ጎርጎራ ኢኮ ሎጅ የሚደረገውን ጉዞ ይበልጥ ምቹ አድርጋው ሰንብታለች።
አሁን ደግሞ ጣና ነሽ ፪ ጀልባ የመጀመሪያውን የመንገደኞች ማጓጓዝ ከባሕር ዳር ወደ ደልጊ እና ደቅ በማድረግ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ጀምራለች።
በሳሙኤል ወርቃየሁ
#ebcdotstream #bahirdar #tananeshII #ጣናነሽ፪