20ኛውን የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ በወልቂጤ ከተማ የተዘጋጀውን ሀገር አቀፍ የንግድ ኤግዚቢሽንና ባዛር፤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መርቀው ከፍተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኤግዚቢሽንና ባዛሩ የክልሉን ባህልና እሴቶች ለማስተዋወቅ እንዲሁም የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ከማገዙም ባሻገር፤ በጋራ እሴቶች ላይ የተገነባ ዴሞክራሲያዊ መግባባትን ለመፍጠር አይነተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
በወልቂጤ ስታዲየም በተዘጋጀው በዚህ ኤግዚቢሽንና ባዛር ላይ፤ የክልሉን ባህል የሚያንፀባርቁ የዕደ ጥበብ ውጤቶች፣ ባህላዊ ምግቦች፣ ወካይ ቅርሶች፣ እንዲሁም የግብርና ምርቶች፣ አልባሳት እና የተለያዩ ቁሳቁሶች ቀርበውበታል።
በመርሐ ግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
በመስከረም ቸርነት