Search

በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እና የድንበር ቁጥጥር ላይ ትብብርን ለማጠናከር ያለመው ስምምነት

ዓርብ ኅዳር 26, 2018 74

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እና የድንበር ቁጥጥር ዙሪያ ከአጋር አካላት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን ስምምነት አከናውኗል።

ስምምነቱ የሰው ሀብት ልማት፣ የድንበር ጥበቃ ክህሎት ስልጠና እና መሰል ተግባራትን በተጠናከረ መልኩ ለማከናወን ያግዛል ተብሏል።

ለስምምነቱ ተግባራዊነት የዓለም የስደተኞች ድርጅት (IOM)፣ ኔዘርላንድስ፣ ስዊዘርላንድ፣ ጀርመን እና ሌሎች አካላት ድጋፍ እንደሚያደርጉ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስታውቋል።

የፕሮጀክቱ ምዕራፍ አንድ ትግበራ ከሜይ 2024 እስከ ጁን 2025 የተከናወነ ሲሆን፤ በዚህም አመርቂ ውጤት መገኘቱ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ ሁለተኛ ምዕራፍ ትግበራም ለቀጣይ ሁለት ዓመታት የሚዘልቅ መሆኑ ተጠቅሷል።

ይህም ኢትዮጵያ እያከናወነችው ያለውን የሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እና የድንበር ቁጥጥር ተግባር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር ስለመሆኑም ተገልጿል።

በሳምሶን በላይ

#EBC #ebcdotstream #immigration #ICSEthiopia #IOM