የፌዴሬሽን ምክር ቤት ኅብረ ብሔራዊነት እንዲደምቅ አስተዋፅኦ ላደረገው የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢቢሲ) ዕውቅና ሰጥቷል።
ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በድምቀት እንዲከበር ለዝግጅቱ አስተዋፅኦ ላደረጉ አካላት ዕውቅና ሰጥቷል።

የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ለክልል ምክር ቤቶች የተዘጋጀውን ዕውቅና ያበረከቱ ሲሆን፤ በዓሉ በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር ለተደረገው ዝግጅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ለነበራቸው የፌዴራል የፀጥታ አካላትም ዕውቅና ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የተለያዩ የፌዴራልና የክልል ተቋማት እንዲሁም የግል ድርጅቶች ዕውቅና የተሰጣቸው ሲሆን፣ የዘንድሮውን ክብረ በዓል በድምቀት ላዘጋጀው ለማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷል።
በሌላ በኩል አስተናጋጁ ክልል ለበዓሉ ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ክልሎች እና የተለያዩ አካላት የክልሉን ባህልና እሴት የሚገልጹ ልዩ ሽልማቶችን አበርክቷል።
በለሚ ታደሰ