ከ25 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ተደራሽ የሚሆኑበት ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ሊካሄድ ነው።
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው፥ ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻው ከታህሳስ 3 እስከ 6 ይካሄዳል።
ዘመቻውን አስመልክቶ ሀገራዊ የንቅናቄ መድረክ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል።
በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የበሽታዎች ቅኝትና ቅድመ ማስጠንቀቂያ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ እንዳለ ዘመነ፥ ፖሊዮን ለማጥፋት የተቀናጀ ሀገር አቀፍ የክትባት ዘመቻ በመላው ሀገሪቱ ተግባራዊ እንደሚደረግ ጠቁመዋል።
ለዚህም በሁሉም ክልሎች የክትባቱ ቁሳቁስና ተያያዥ ግብዓት አቅርቦትን ጨምሮ ቅድመ ዝግጅት በበቂ ደረጃ እየተደረገ እንደሚገኝ ተጠቅሷል።
በዘመቻው ክትባቱ በዋናነት ዕድሜያቸው ከ5 በታች ለሆኑ ህጻናት የሚሰጥ ሲሆን፤ የቤት ለቤት የፖሊዮ ክትባት ከመስጠት ጎን ለጎን የበሽታውን ምልክት ያሳዩ ሕፃናትን የመለየት ሥራ እንደሚከናወን ተገልጿል።
በጤና ሚኒስቴር የክትባት ፕሮግራም የኮሙኒኬሽን አማካሪ ወይዘሮ ፀጋነሽ ገድሉ በበኩላቸው እንዳሉት፥ በዘመቻው መደበኛ የፖሊዮ ክትባት ያልወሰዱ ሕፃናት ይካተታሉ።
በ4 ቀናት ውስጥ ክትባቱ በሁሉም ክልሎች እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትብብር ማድረግ እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል።
በአባዲ ወይናይ
#ebcdotstream #Ethiopia #polio #vaccine