Search

“ከባዕዳን ኃይሎች ጋር በመተባበር የሚፈፀም የጥፋት ተልዕኮ ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ አይጠቅምም” - የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት

ሓሙስ ታኅሣሥ 02, 2018 69

ከቀድሞው ሕወሓት፣ ሻዕቢያ እና ግብጽ ጋር በትብብር የሚፈፀም የጥፋት ተልዕኮ ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም አይደለም ሲል የአማራ ፋኖ ሕዝባዊ ድርጅት (አፋሕድ) ገለጸ።

የአፋሕድ ኃላፊዎች የሰላም ስምምነቱን አስመልክተው ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

በአፋሕድ የጎጃም ዕዝ የፋይናንስ ኃላፊ ከፋለ ዓለሙ፥ ከቀድሞው ሕወሓት፣ ሻዕቢያ እና ግብጽ ጋር በመተባበር የሚፈፀም የጥፋት ተልዕኮ ለአማራ ሕዝብም ሆነ ለኢትዮጵያ የሚጠቅም አይደለም ብለዋል።

ሕዝባችን ከዚህ በላይ ጦርነት መሸከም አይችልም ያሉት ኃላፊው፤ ድርጅቱ ኢትዮጵያን ጥለው ከሻዕቢያ እና ግብጽ ጋር በመተባበር ሀገር ለመበተን ከሚፈልጉ ኃይሎች ጋራ መሥራት እንደማይፈልግ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል መንግሥት እና በድርጅቱ መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነትም የአማራን ሕዝብ ክብር እና የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ባስጠበቀ መንገድ የተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል።

በሰላም ስምምነቱም ድርጅቱ የተሳሳተውን የውክልና ጦርነት በመተው ትክክለኛውን የሰላም አማራጭ መከተሉን ተናግረዋል።

ሌሎች የታጠቁ አካላትም የሀገርን እና የሕዝብን ጥቅም በሚያስከብር አግባብ የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።