Search

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ለሐገረ መንግስት ግንባታ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ

ሰኞ ታኅሣሥ 06, 2018 74

ሀገር የሚገነባው በጥበብ እንደመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች በስራዎቻቸው ለሐገረ መንግስት ግንባታ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ጥሪ አቀረቡ።

ሚኒስቴሩ የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ረቂቅ ፖሊሲ መነሻ ሰነድ ላይ ከዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ሲያደርግ የነበረው የምክክር መድረክ ተጠናቅቋል።

በመድረኩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፤ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ለኪነ ጥበቡ ትኩረት በመስጠት ለዘርፉ እድገት የሚያግዙ በርካታ ማዕከሎች እየተገነቡ ይገኛሉ ብለዋል።

አሁን ደግሞ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የጥበባት እና ፈጠራ ኢንዱስትሪ ፖሊሲ በማዘጋጀት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል።

ይህም የመደመር መንግሥት ለዘርፉ የሰጠውን ትኩረት በተግባር ያረጋገጠበት ነው ብለዋል።

ሚኒስትሯ አክለውም፤ የዘርፉ ባለሙያዎች መንግስት ባስቀመጣቸው በተለይ የሕዝብን አንድነትና ትስስር በሚያጠናክሩ እንዲሁም አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡  

በዘአማኑኤል መንግሥቱ

#Ebc #Ebcdotstream #Ethiopia #art #policy