Search

በመዲናዋ እየተስፋፉ የመጡት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች

ማክሰኞ ታኅሣሥ 07, 2018 653

ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን በመጠቀም አረንጓዴ ኢኮኖሚን እየገነባች ትገኛለች።

በመሆኑም እንደ ሀገር አካባቢን የማይበክሉ እና የውጭ ወጪን ምንዛሬን የሚያስቀሩ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ወደ ሀገር ማስገባት ከተጀመረ ሰንበትበት ብሏል።

የኤሌክትሪክ መኪኖች እንደ ሀገር መበራከታቸውን ተከትሎ የኃይል መሙያ ጣቢያዎችም እየተበራከቱ ይገኛሉ።

ኢትዮ ቴሌኮም በአዲስ አበባ ከከፈታቸው 3 የኃይል መሙያ ጣቢያዎች በተጨማሪ የተለያዩ ባለሀብቶችም ወደ ዘርፉ በመግባት የኤሌክትሪክ መኪኖችኃይል መሙያ ጣቢያዎችን እያስፋፉ ይገኛሉ።

ኢቲቪ ያነጋገራቸው የኤሌክትሪክ መኪኖች አሽከርካሪዎች እየተስፋፋ በመጣው አገልግሎት ተጠቃሚ ስለመሆናቸው ገልጸዋል።

ኃይል መሙያ ጣቢያዎች መስፋፋት የኃይል አቅርቦት ለማግኘት እንዳይቸገሩ እና ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ እንዳስቻላቸውም ነው የተናገሩት።

በከተማዋ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እያደገ በመሆኑ፤ ኃይል መሙያ ጣቢያዎች ቁጥርም በዚህ ልክ ማደግ እንዳለበት አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

በሜሮን ንብረት 

#EBC #ebcdotstream #greeneconomy #electricvehicle #ev