Search

ለሥርዓተ ፆታ እኩልነት መረጋገጥ መሠረት ሆኖ የሚያገለግለው ፋይዳ መታወቂያ

ማክሰኞ ታኅሣሥ 07, 2018 33

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ለሥርዓተ ፆታ እኩልነት መረጋገጥ መሠረት ሆኖ እንደሚያገለግል የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና አስተባባሪ ዮዳሔ አርዓያሥላሴ ተናገሩ።

ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የብሔራዊ መታወቂያ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያለመ የሴቶች ንቅናቄ መካሄድ ጀምሯል።

በንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረኩ የተገኙት አቶ ዮዳሔ፥ የፋይዳ ምዝገባን ተደራሽ ለማድረግ የሴቶች ሚና ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል።

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ ሂክማ ኸይረዲን፥ የመታወቅ መብትን አረጋግጦ ሴቶች በኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል ረገድ የፋይዳ መታወቂያ ትልቅ ሚና እንደሚጫወት አስገንዝበዋል።

ከዚህ ቀደም ሴቶች ከመታወቅ መብታቸው ተገልለው የመታወቂያ ባለቤት የነበሩት ጥቂቶች ብቻ እንደነበሩ ያነሱት ሚኒስትር ዴዔታዋ፤ በዚህ ሳቢያ በፍትሕ እና ፋይናንስ ዘርፎች ተጠቃሚ ሳንሆን ቀርተናል ብለዋል።

ዛሬ ላይ ከብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመሆን በተከናወነው ሥራ ከ30 ሚሊዮን የብሔራዊ መታወቂያ ባለቤቶች ውስጥ 40 በመቶዎቹ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸዋል።

አቶ ዮዳሔ በበኩላቸው፥ ሴቶች ካላቸው ሀገራዊ ፋይዳ አንፃር 40 በመቶ ትንሽ መሆኑን ገልጸው፤ 50 በመቶን መሻገር እንዳለበት ተናግረዋል።

በዘንድሮው ዓመት 90 ሚሊዮን ዜጎችን የብሔራዊ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ እየተሠራ እንደሚገኝ በመድረኩ ተገልጿል።

በሳምሶን ገድሉ

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #nationalid #genderequality