Search

ለዓለም አቀፍ ጉባኤዎች ተመራጭ የሆነችው አዲስ አበባ

ዓርብ ታኅሣሥ 10, 2018 33

አዲስ አበባ ከፍተኛ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉባኤዎችን በብቃት በማስተናገድ ረገድ ያዳበረችው የካበተ ልምድ፣ ለአፍሪካ ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጭምር ቁልፍ የመገናኛና የውሳኔ ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል።
የአፍሪካ ኩራት የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያለው ሰፊ የአየር ትስስርና የአገልግሎት አቅምም ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ስኬት ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።
በተጨማሪም ከተማዋ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችና ዘመናዊ የኮንፈረንስ ማዕከላት ያሉባት በመሆኑ፣ ለታላላቅ ስብሰባዎች የሚመጡ እንግዶችን በላቀ የጥራት ደረጃ ለመቀበልና ለማስተናገድ የሚያስችል ሙሉ ዝግጁነት አላት።
ይህም አዲስ አበባን በዓለም አቀፍ መድረኮች ዘንድ ተዓማኒና ተመራጭ መዳረሻ አድርጓታል።
 
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ የተከናወኑት የውበትና የኮሪደር ልማት ሥራዎች አዲስ አበባን ለስብሰባዎች ብቻ ሳይሆን ለቱሪዝም ዘርፍም ይበልጥ ማራኪ እያደረጓት ነው።
በከተማዋ የተገነቡት አዳዲስ ፓርኮች፣ ሙዚየሞችና የታሪክ መዳረሻዎች ለስብሰባ የሚመጡ እንግዶች ከሥራቸው ጎን ለጎን የከተማዋን ውበት፣ ባህልና ታሪክ እንዲረዱ ሰፊ ዕድል ፈጥሯል።
ይህ የተቀናጀ ልማት ከተማዋን የጉባኤ ቱሪዝም (MICE Tourism) ማዕከል በማድረግ በዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት ከፍ እንዲል እያደረገው ይገኛል።
እስካሁን የታየው የጉባኤዎች መስተንግዶ ስኬትና የተመዘገበው የዲፕሎማሲ ልምድ፣ ከተማዋ በቀጣይም ለታላላቅ ዓለም አቀፍ ውሳኔዎችና ውይይቶች ዋነኛ መዳረሻ ሆና እንድትቀጥል የሚያስችላት መሆኑን ዓለም አቀፍ እንግዶችም ጭምር የመሰከሩት ሀቅ ነው።