በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን፣ መተማ ወረዳ እንዲሁም ማዕከላዊ ጎንደር ዞን፣ ጎንደር ዙሪያ ወረዳ የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርገው ሲቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ከነሙሉ ትጥቃቸው በሰላም ገብተዋል።
ታጣቂዎቹ ሲገቡ በዞን፣ በወረዳ እና በመከላከያ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በሀገር ሽማግሌዎች ደማቅ አቀባበል እንደተደረገላቸው ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
እስካሁን በዱር በገደሉ ያለአግባብ ስንገላታ ቆይተናል ያሉት ታጣቂዎቹ፤ ሌሎች በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎችም የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እንዲገቡ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለየአካባቢያቸው ዘላቂ ሰላምና ልማት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸው፤ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የበደልነውን ህዝብ ለመካስ ተዘጋጅተናል ብለዋል።
#EBC #ebcdotstream #AmharaRegion #peace #disarmament