የአማራ ክልል ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሹመቶችን በማፅደቅ ዛሬ አጠናቅቋል።
1. አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ/ር)፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ
2. ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር)፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የገጠር ልማት ዘርፍ አስተባባሪ
3. ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር)፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የማኅበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ
4. አማኑኤል ፈረደ (ዶ/ር)፦ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል የአስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ

5. መንገሻ ፈንታው (ዶ/ር)፦ የአማራ ክልል ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
6. ደረጀ ማንደፍሮ፦ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ
7. ጥላሁን ወርቅነህ፦ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ
8. ሞላ መልካሙ (ዶ/ር)፦ የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ
9. ኢንጅነር ዳኝነት ፈንታ (ዶ/ር)፦ የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጅ ቢሮ ኃላፊ
10. አታላይ ጥላሁን፦ የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ
11. ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር)፦ የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሐብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
12. እሸቱ የሱፍ (ዶ/ር)፦ የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ
13. ዓባይ መንግሥቴ፦ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
በተጨማሪም ምክር ቤቱ የ174 የወረዳ ፍርድ ቤቶች ዳኞችን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን፤ ከተሿሚ ዳኞች መካከልም 33ቱ ሴቶች ናቸው።
ምክር ቤቱ ሁለት ቀናት በፈጀ ጉባኤው በተያዘው በጀት ዓመት በክልሉ ትምህርት ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን እንዲሁም የክልሉ ዋና ኦዲተር የኦዲት ሪፖርቶችን ገምግሟል።
በተጨማሪም የክልሉ የፕሮጀክት አስተዳደርና አመራር ሥርዓት መወሰኛ፣ የኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያ፣ የመንግሥት ሠራተኞች አስተዳደር ማሻሻያ፣ የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ማሻሻያን ጨምሮ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን አፅድቋል።
በሳሙኤል ወርቃየሁ
#EBC #ebcdotstream #AmharaRegion #appointments