Search

ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚካሄደው "የኮንስትራክሽን ምህንድስናና ማኔጅመንት የልህቀት ማዕከል" ግንባታ

ቅዳሜ ታኅሣሥ 18, 2018 117

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት እያስገነባ የሚገኘውን የኮንስትራክሽን ምህንድስናና ማኔጅመንት የልህቀት ማዕከልን የመስክ ምልከታ አካሂደዋል።
ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሰንዳፋ ከተማ አቅራቢያ እየተገነባ ያለው ይህ የልህቀት አካዳሚ ግንባታው ሲጠናቀቅ ኢንዱስትሪውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያስችላል ተብሏል።
በተለይም ተወዳዳሪ ባለሙያዎችን በማፍራት፣ በኮንስትራክሽን ዘርፉ ላይ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮችን በመምራት ዘርፉ ላይ ያሉ ችግሮችን መቅረፍ እንደሚያስችል ተገልጿል።
የኢኒስቲቲዩቱ ግንባታ በተጀመረ በ11 ወራት ውስጥም በከፍተኛ ፍጥነት እየተከናወነ እንደሚገኝ ቋሚ ኮሚቴው አባላት ገልፀዋል።
 
ብሩክታዊት ተገኝ