የ2026 አዲስ ዓመት መግባትን በማስመልከት በለንደን የቴምስ ወንዝ ዳርቻ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች እና ጎብኚዎች በተገኙበት ደማቅ የሙዚቃ ዝግጅት የተካተተበት የአዲስ ዓመት አቀባበል ሥነሥርዓት ተካሂዷል።
12 ሺህ ርችቶች የለንደንን ሰማይ ሲያደምቁ ባመሹበት በዚህ የአዲስ ዓመት አቀባበል ሥነሥርዓት፣ 420 የሚሆኑ ድሮኖች በልዩ ሁኔታ የተቀነባበሩ ዲጂታል ምስሎችን እና የመልካም ምኞት መግለጫዎችን በሰማይ ላይ ሲያሳዩ አምሽተዋል።
ከታዋቂው የቢግ ቤን (Big Ben) የደወል ድምፅ ጋር ተቀናጅቶ ለ12 ደቂቃዎች ያህል ሲተኮስ የቆየው ይህ የርችት ትርዒት፣ በተጠቀመው የርችት ብዛት በአውሮፓ ተወዳዳሪ እንደሌለው የተገለፀ ሲሆን፣ በቴምስ ወንዝ ላይ ከቆሙ 3 ግዙፍ ጀልባዎች ላይ በአጠቃላይ 12 ሺህ ርችቶች ተተኩሰዋል።
በዋሲሁን ተስፋዬ
#EBCdotstream #Europe #London #newyear #fireworks #RiverThames