Search

የ117 ዓመቷ ብሪታንያዊት ኤተል ካተርሃም የዓለማችን እድሜ ጠገብ ሴት በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዘገበች

ዓርብ ነሐሴ 15, 2018 57

117 ዓመቷ ብሪታንያዊት ኤተል ካተርሃም በሕይወት ያሉ የዓለማችን እድሜ ጠገብ ሴት በመሆን አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ያስመዘገበች ሲሆን፣ 117 ዓመት ልደቷን በማክበርም ይህንን ዕድሜ ያየች የመጀመሪያዋ ብሪታንያዊት ሴት ሆናለች።

በነሐሴ 1909 በሃምፕሻየር የተወለደችው ካተርሃም፣ 2025 የብራዚላዊቷ ኢና ካናባሮ ሉካስ ህልፈትን ተከተሎ በሕይወት ያለች የዓለማችን እድሜ ጠገብ ሰው ማዕረግን ተረክባለች።

የልደት በዓሏ በሰሪ በሚገኘው የሙሪያን መንከባከቢያ ማዕከል በደመቀ ሁኔታ የተከበረላት ሲሆን፣ የማዕከሉ ሠራተኞችም ለክብሯ ሲሉ የማዕከሉን አትክልት ስፍራየኤተል አትክልት ቦታበማለት ሰይመውላታል።

በሰው ልጅ የተመዘገበ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ዕድሜ ከደረሱ ጥቂት ሰዎች አንዷ የሆነችው ካተርሃም፣ 1900 እስከ 1909 ባለው ዘመን ተወልደው በሕይወት ካሉት ሰዎች መካከልም የመጨረሻዋ ናት።

ከአንድ ክፍለ ዘመን በላይ በሚሻገረው ረጅም የሕይወት ጎዳናዋ ሁለቱን የዓለም ጦርነቶች አሳልፋለች፤ ስድስት የብሪታንያ ነገሥታትን ከመመልከቷም በላይ 110 ዓመቷ ኮቪድ-19 አሸንፋ 116 ዓመት ልደቷ በንጉሥ ቻርልስ ሣልሳዊ በአካል ተጎብኝታለች።

በወጣትነቷ በብሪቲሽ ሕንድ በሞግዚትነት የሰራችውና በኋላም ከባሏ ጋር በጊብራልታር እና በሆንግ ኮንግ በመኖር የእንግሊዝኛ ቋንቋ መዋለ ሕፃናት መስርታ የነበረችው ይህች ድንቅ እናት፣ ለአንድ ክፍለ ዘመን ለዘለቀው ረጅም ዕድሜዋ ምስጢሩን ስትጠየቅነገሮችን በረጋ መንፈስ መውሰድ፣ ሰላምን መጠበቅ እና ከማንም ጋር አለመከራከርእንደሆነ ትመክራለች።

በሲሳይ መንግስቱ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: