በምስራቅ ቻይና ዢጂያንግ ግዛት በምትገኘው ዮንግካንግ ከተማ፣ የትራፊክ ፍሰትን የመቆጣጠር እና የማስተካከል ስራ የሚያግዝ የሮቦት ትራፊክ ፖሊስ የመጀመሪያ የሙከራ ስራውን በይፋ ጀምሯል።
ይህ የቴክኖሎጂ ድንቅ ውጤት የሆነው ሮቦት ለ30 ደቂቃ ብቻ በመብራት ከተሞላ በኋላ ለአራት ሰዓታት ያህል ያለምንም እረፍት በተከታታይ መስራት የሚችል ነው።
የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው የመንገድ መገናኛዎች ላይ የሚከናወኑ መደበኛና ተደጋጋሚ ተግባራትን በብቃት ለማከናወን ተቀርጾ የተሰራ ነው።
ሮቦቱ በተለይም አሽከርካሪዎችንና እግረኞችን በስርዓት የመምራት፣ የመንገድ ላይ ደህንነት ማሳሰቢያዎችን የመስጠትና በትራፊክ መጨናነቅ ወቅት የትራፊክ ፖሊሶችን ስራ በከፍተኛ ደረጃ የማቃለል ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።
ይህ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የሮቦቲክስ ቴክኖሎጂ ውጤት የከተሞችን የመንገድ ደህንነትና የትራፊክ አስተዳደር ወደ አዲስ የዘመናዊነት ደረጃ የሚያሸጋግር ድንቅ እርምጃ ተደርጎ ተወስዷል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: