Search

በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ” - የናትናኤል ፒርስ ማስታወሻ

ረቡዕ ታኅሣሥ 29, 2018 99

ከ200 ዓመታት በፊት ከ1805 - 1831 ድረስ ለ13 ዓመታት ያህል በኢትዮጵያ የኖረው እና የራስ ወልደሥላሴ የቅርብ ወዳጅ የነበረው እንግሊዛዊው ናትናኤል ፒርስ በሕይወት ታሪኩ ዙሪያ በጻፈው "የናትናኤል ፒርስ ሕይወትና ጀብዱ" በተሰኘው መጽሐፉ ስለ ገና ጨዋታ ያሰፈረው መረጃ በታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ዛሬም ድረስ የሚጠቀስ ነው።

ፒርስ በዚህ መጽሐፉ በኢትዮጵያ የነበረውን ቆይታ በተመለከተ በርካታ ነገሮችን ያነሳ ሲሆን፤ ከእነዚህ መካከልም ስለ ባህላዊው የኢትዮጵያውያን የገና ጨዋታ የጻፈው ይጠቀሳል።

ለገና ጨዋታ የምትሆነው ኳስ (ሩር) በአብዛኛው ከጠንካራ የግራር ዛፍ ሥር ተጠርቦ እንደሚዘጋጅ፣ በተመሳሳይ "ገና" ተብሎ የሚጠራው መምቻውም በቀላሉ ከማይሰበር ጠንካራ እንጨት እንደሚሠራ የሚጠቅሰው ፒርስ፤ ጨዋታው ከእንግሊዙ ሆኪ ጋር ቢመሳሰልም የገና ጨዋታ ኃይለኛ የጉልበት ፋክክር የሚታይበት መሆኑን ጽፏል።

ጨዋታው ከስፖርታዊ ይዘቱ ባለፈ የነፃነት መድረክ መሆኑን ሲገልፅም፥ "አንድ አገልጋይ አሳዳሪ ጌታውን ወይም ከእርሱ በላይ ያለ ማንኛውም ከፍተኛ ማዕረግ ያለውን ሰው በገና ጨዋታ ወቅት ቢመታው፣ ምንም ዓይነት ቅጣት ሳይደርስበት ወይም እንደጥፋተኛ ሳይቆጠር ጨዋታውን መቀጠል እንደሚችል እና በጨዋታው ወቅት የሚፈጠሩ ግጭቶችና ጉዳቶች ሜዳው ላይ በይቅርታ እንደሚታለፉ፤ ተጫዋቾች በጨዋታው ወቅት የከፋ ጉዳት ቢያጋጥማቸው እንኳን ቂም ሳይዪዙ እና ሳይካሰሱ ከሜዳ እንደሚወጡ፣ ይህም በኢትዮጵያውያን ዘንድ ያለውን የይቅር ባይነት እሴት እንደሚያሳይ ናትናኤል ፒርስ በማስታወሻው አስፍሯል።

በዋሲሁን ተስፋዬ

#EBC #EBCDotstream #EthiopianChristmas #Genna #Hockey #NathanielPearce