ፊፋ እና የፈረንሳዩ እግር ኳስ መጽሄት በጋራ ባዘጋጁትም ይሁን ተነጣጥለው የዓመቱ ምርጥ ተጫዋች ዕውቅናን በሰጡባቸው ዓመታት ቅሬታዎች የተነሳባቸውም በርካታ ናቸው፡፡ በተለይ ደግሞ የምርጫ ሂደቱ ወጥነት የጎደለው መሆኑ የክርክር በር እንዲከፍት አድርጓል፡፡

በዋናነት ጥያቄ ከሚነሳባቸው የባሎንዶር ሽልማቶች በቀዳሚነት የሚቀመጠው ይሄ ነው፡፡ ይሄ ዓመት ለስፔናዊው አማካይ ፍጹም የተለየ ቢሆንም ያሸነፈው ሊዮኔል ሜሲ ነው፡፡ ኢኔሽታ በግሉም ከቡድኑም ጋር ምርጥ ጊዜ አሳልፏል፡፡ በእርግጥ አንድሬስ ኢኔሽታ እና ሊዮኔል ሜሲ አንድ ክለብ ውስጥ የነበሩ በመሆናቸው በቡድን ተመሳሳይ ክብር አሳክተዋል፡፡
ነገር ግን ኢኔሽታ በአፍሪካ ምድር ለመጀመርያ ጊዜ በተደረገው የዓለም ዋንጫ ከስፔን ጋር ሻምፒዮን ሲሆን በፍጻሜው ሆላንድ ላይ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረውም ራሱ ኢኔሽታ ቢሆንም የባሎንዶር ክብርን የወሰደው ግን በተሰለፈባቸው 53 ጨዋታዎች 47 ግቦችን ያስቆጠረው ሊዮኔል ሜሲ ነው፡፡
በዚሁ ዓመት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግን ከኢንተር ሚላን ጋር ያሳካው እና ለዓለም ዋንጫ ፍጻሜ የደረሰው ዊሽኒ ሽናይደር እንዲሁም የባርሴሎናው አማካይ ዣቪ ሄርናንዴዝም በግላቸውም ከቡድናቸውም ጋር የተለየ የውድድር ዓመት ያሳለፉ ተጫዋቾች ናቸው፡፡

ይሄ ዓመት የጁቬንቱሱ አማካይ ፓቭል ኔድቬድ ባሎንዶርን ያሸነፈበረት ነው፡፡ እንደ ዚነዲ ዚዳን እና ፓውሎ ማልዲኒ አይነት ከዋክብት ዕጩ ሆነው በቀረቡብት ምርጫ በዓመቱ ካሳለፈው ድንቅ ጊዜ አንጻር ብዙዎች የአሸናፊነት ግምቱን ለቲየሪ ሄንሪ ቢሰጡም ኔድቬድ ተመርጧል፡፡
በውድድር ዓመቱ በግል ባስመዘገቡት ውጤት ሄንሪ ከኔድቬድ በብዙ የተሻለ መሆኑ ደግሞ ውጤቱ ላይ ጥያቄ እንዲነሳበት አድርጓል፡፡ በዚያ ዓመት ፈረንሳዊው አጥቂ በፕሪሚየር ሊጉ ከ20 በላይ ግቦች እና ከ20 በላይ ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን በማቀበል የመጀመርያው ተጫዋች የሆነበት ዓመት ነው፡፡
በተጨማሪም የእግር ኳስ ተጫዋቾች ማኅበር የዓመቱ ምርጥ ተብሎ ሲመረጥ ከሀገሩ ጋር የፊፋ ኮንፌደሬሽን ዋንጫን አንስቷል፡፡ በዚሁ መድረክም የውድድሩ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ በመሆን የወርቅ ጫማ እና እና የውድድሩ ምርጥ ተጫዋች በመሆን የወርቅ ኳስ የተሸለመበት ነበር፡፡ በአጠቃላይ በውድድር ዓመቱ በተሰለፈባቸው 55 ጨዋታች 35 ግቦችን ያስቆጠረው ቲየሪ ሄንሪ ከአርሰናል ጋርም የኤፍ ኤ ዋንጫን ቢያነሳም ባሎንዶርን ለማሸነፍ በቂ ሆኖ አልተገኘም::
የባሎንዶር አሸናፊው ፓቭል ኔድቬድ በዓመቱ ውስጥ በአጠቃላይ 14 ግቦችን ሲያስቆጥር 17 ለግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል፡፡ በዓመቱ ውስጥ የሴሪኤውን እና የጣልያን ዋንጫን ያነሳው ኔድቬድ በሻምፒዮንስ ሊግ ለፍጻሜ የደረሰበት ትልቁ ውጤቱ ነው፡፡

በዚህ ዓመት ፈረንሳዊው የመስመር ተጫዋች ከሙኒክ ጋር የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ጨምሮ አራት ክብሮች አሳክቷል፡፡ ሙኒክ ለፍጹምነት የቀረበ ዓመት ባሳለፈበት 2013 የባለንዶር አሸናፊ የነበረው ግን ክርስቲያኖ ሮናልዶ ነው፡፡ ሪቤሪም ከሽልማት ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ባሎንዶርን ተነጥቄአለሁ የሚል ሃሳብ ሰጥቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ከማድሪድ ጋር ትልቅ ዋንጫ ማንሳት ባይችልም በግሉ በተሰለፋባቸው 55 ጨዋታዎች 55 ግቦችን አስቆጥሯል፡፡ በዚሁ ዓመት ሌላኛው የባየር ሙኒክ ተጫዋች የነበረው አርያን ሮበንም ከሪቤሪ እኩል አራት ዋንጫዎችን ያሳካበት አመት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ፖላንዳዊው ዓጥቂ በዚህ የውድድር ዓመት ከባየር ሙኒክ ጋር ከሻምፒዮንስ ሊግ ውጭ ሁሉንም ዋንጫዎች አሳክቷል፡፡ በግሉም ምርጥ ጊዜ ያሳላፈው አጥቂ በተሰለፈባቸው 47 ጨዋታዎች 55 ግቦችን ቢያስቆጥርም በጊዜው ተከስቶ በነበረው የኮቪድ ወረርሽኝ የፈረንሳዩ የእግር ኳስ መጽሄት ሽልማቱን በመሰረዙ ትልቁ ክብረ እንዲያልፈው ሆኗል፡፡
የዓለም ዋንጫ አናፊው ጂያንሉጂ ቡፎን በ2006 ባሎንዶር በሀገሩ ልጅ ፋቢዮ ካናቫሮ የተወሰደበትን ጨምሮ አንድሪያ ፒርሎ፣ ስቴቨን ጀራርድ፣ ኔይማር፣ ዴኒስ ቤርካምፕ፣ ሊዩስ ስዋሬዝ እና ዝላታን ኢብራሂሞቪች ምርጥ ጊዜ ባሳለፉባቸው ዓመታት ለትልቁ ክብር ካልታደሉ ከዋክብት መካከል ናቸው፡፡
በአንተነህ ሲሳይ