Search

ጎንደር በአርቆ አሳቢና በታሪክ ሠሪ መሪዎቿ ዳግም ወደ ታሪካዊ ከፍታዋ እየተሻገረች ነው - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ

እሑድ ጥር 10, 2018 103

ሙሽሪት ጎንደር አመሥግናለች! ፤ ዓይናሚት ጎንደር በሰርጓ ዕለት ያስዋቧትንና ዳግም ቀና እንድትል ያደረጓትን ሁሉ ዛሬ አመሥግናለች ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
አቶ ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ የትስስረ ገጽ እንዳሰፈሩት፤ የነገሥታት መናገሻ፣ የኅብር ኢትዮጵያውያን መኖሪያ፣ የስልጣኔ ማዕከል የሆነቸው ጎንደር በአርቆ አሳቢና በታሪክ ሠሪ መሪዎቿ ዳግም ወደ ታሪካዊ ከፍታዋ እየተሻገረች ነው ብለዋል።
በአፄ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት እድሳትና በኮሪደር ልማት ተውባለች፤ ከጧት እስከ ማታ ሳትደበዝዝ ፈክታለች ሲሉም ገልጸዋል።
አቶ ተመስገን ጥሩነህ ፤ የጎንደር ከተማ አስተዳደር እና ወጣቶች ለሰጣችሁን ልዩ ሽልማትና እውቅና ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል።