Search

ጥምቀት ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ቅዱስ እና ውድ ስጦታ ነው - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ

ሰኞ ጥር 11, 2018 52

ጥምቀትን በጎንደር ያከበሩት የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፥ በከተማዋ ጥምቀትን ሲያከብሩ ከነበሩ ቱሪስቶች ጋር በመገናኘቴ በእጅጉ ተደስቻለሁ ብለዋል።

በዙዎቹ ቆይታቸው እጅግ የተለየ እና መንፈሳዊ እርካታን የሚያጎናጽፍ እንደነበር ገልጸውልኛል ብለዋል ፕሬዚዳንት ታየ በማኅበራዊ ትስስር መተግበሪያው ኤክስ ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ።

ልዩ ሃይማኖታዊ እና ታሪካዊ ቅርስ የሆነው የጥምቀት በዓል በእርግጥም ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችው ቅዱስ እና ውድ ስጦታ ነው ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።

#EBC #ebcdotstream #Ethiopia #Timket #Gondar #TayeAtskeSelassie